ጤና ይስጥልኝ እንኩዋን ደህና መጡ የቴክኖሎጂ ድረ ገጽ Hola, bienvenido pagina web de la tecnologia Hello, welcome web page of technology







129ኛዉ የአድዋ ድል በዓል ኢትዮጵያኖች እያከበሩት ነዉ
129ኛዉ የአድዋ ድል በዓል ለኢትዮጵያኖች ለአሁኑ ትዉልድ ትልቅ ትርጉም አለዉ በዛን ወቅት ለነጻነት በተደረግ ጦርነት አያቶቻችን በንጉሥ ሚኒሊክ እና በብልሁዋ ጣይቱ አዝማችነት ዘር ሃይማኖት ጾታ አካባቢ ሳይለዩ ከ 1000 ኪሜ በላይ በእግር በመጉዋዝ ሃገራችንን ከወቅቱ የቅኝ አገዛዝ በማትረፍ ዛሬ የምናያትን ትልቅ እና የነጻነት ተምሳሌት ሃገር አስረክበዉናል።
በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በየቦታዉ እዚህም እዚያም ያለዉን መናቆርን እና መፋተግ አሽቀንጥሮ በመጣል ሰላምን በማስፈን እና በመስራት መበልጸገና ከድህነት መዉጣት ይቻላል፣ እድሜ ለነዛ ለነጻነታቸው ቀናኢ ለሆኑ ቆፍጣና አባቶቻችን ሰርተን ልንጠቀምበት የሚያስችል በሁሉም የሃገራችን አካባቢ እና ለሁላችንም ተርፎ የሚዛቅ የተትረፈረፈ እምቅ ሃብት አቆይተውልናል።
እናም አያቶቻችንን እያመሰገንን ጠንክረን እንስራ።

አድዋ Adwa ምንሊክ ጣይቱ
በሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ላይ የሌሊት ንጋት ውበት ፡ አስደናቂ የተፈጥሮ ስጦታ
ስፔን በአውሮፓ በ2024 ዋንጫ ጨፈረች።

ፋያ ቫሌንስያና 2024
በቫሌንሲያ ውስጥ በጣም ቆንጆ ቀናቶች። ከመጋቢት 1 እስከ 19




በቫሌንሲያ ውስጥ በጣም ቆንጆ ምሽቶች። ከመጋቢት 1 እስከ 19
ነፃ የአማርኛ ቋንቋ በስፓኒሽ ክፍል 2

ህዳሴ ግድብ
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ሥራ ተጠናቀቀ

የኛ ትንሿ የዕረፍት ጊዜ
ከብዙ ውይይቶች በኋላ እና ኢኮኖሚያዊ እና ጥራት ያላቸውን በርካታ አማራጮችን አይተን ለ 7 ቀናት አነስ ያለ የእረፍት ጊዜ ለማድረግ ወሰንን ።
ተጨማሪ ያንብቡ

ለኦሺንጌት ቲታን ተጉዋዥ ሰዎች ጉዙዋቸዉ በአሰቃቂ ሁኔታ ተጠናቁዋል
እ.ኤ.አ. በ1912 የሰመጠችዉን ታይታኒክን መርከብን ለመጎብኘት ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ጥልቀት የተግዋዙት አምስቱ ሰዎች ሰርጓጅ መርከብ ወደ “አሰቃቂ ኢምፕሎዥን” ውስጥ በመግባቱ ህይዎታቸዉ ማለፉን የዩኤስ የባህር ጠረፍ ጥበቃ ቢሮ አማካኝነት ተገልጹዋል ።
በኦሽን ጌት ታይታን ውስጥ ይገኙ የነበሩት 5 ዓምስቱ አባላት በርካታ የጊነስ ሪከርዶች ያሉት እንግሊዛዊ አሳሽ፣ የውቅያኖስ ጌት ፕሬዝዳንት፣ የፓኪስታን ተወላጅ እንግሊዝ አባት እና ልጅ እና ታዋቂ ሳይንቲስት በታይታኒክ ላይ ከቀዳሚዎቹ ኤክስፐርቶች አንዱ እንደሆኑ ይቆጠራሉ።
ይህ ለቤተሰቦቻቸው እና የመጥፋቱ ዜና ከተገለጸበት እሑድ 06-20-2023 ጊዜ ጀምሮ ይህንን ለሚከታተል ሁሉ ትልቅ አሳዛኝ ዜና ነው።
ወደ ሰመጠችዉ ታይታኒክ የተጉዋዙት 5ቱ የጉብኝቱ አባላት እስካሁን አድራሻቸው አልተገኘም።
በአትላንቲክ ውቅያኖስ 4000 ሜ ጥልቀት አካባቢ ሰምጣ ወደምትገኘው ታይታኒክ መርከብ በ OceanGate TITAN ያቀኑት 5ቱ የጉብኝት ቡድኞች አባላት እሑድ 06-20-2023 ግንኙነታቸዉ ከተቁዋረጠ ጀምሮ እና ዜናዉ በሰፊዉ ከተሰራጨ በኋላ እስካሁን አልተገኙም ፍለጋውም ቀጥሏል ።
ተጨማሪ ያንብቡ
የግድቦች ግንባታ
ግድቦች መገንባት የውሃ ቁጥጥር እና የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት በሲቪል ምህንድስና እድገት ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ። በታሪክ ውስጥ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን እና የላቁ ቴክኒኮችን በመጠቀም አስደናቂ ግድቦች በመላው ዓለም ተሠርተዋል።

ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
1ª Entrega de mini curso básico de
idioma
amárico en español
አማርኛ በእስፓንሽ ቁዋንቋ መሰረተ ትምህርት
የአማርኛ ቁዋንቋ
ኢትዮጵያ በዓለማችን ላይ ለቋንቋቸው የራሳቸው ፊደል ካላቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ስትሆን ይህ ትልቅ የፊደል ቅርስ ተጠብቆ የቆየው አባቶቻችን ባደረጉት ጥረትና ትጋት ነው።


አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከ ChatGPT ጋር መሰረታዊ ግንኙነትን ለማዳበር የቀርበ ስልጠና
ቴክኖሎጂ
ዛሬ ስለ ቴክኖሎጂ እንነጋገራለን
ቴክኖሎጂ ከቅርብ አሥርተ ዓመታት ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ አድጓል እናም በአኗኗራችንን፣ ሥራችንን እና መስተጋብርን ለውጧል። ከመጀመሪያው የሞባይል ስልክ ከተፈጠረበት ጀምሮ እስከ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ድረስ ቴክኖሎጂ በህብረተሰባችን ላይ ትልቅ ተጽእኖ በማሳደር ለሰው ልጅ እድገት አዳዲስ እድሎችን ፈጥሯል።
ተጨማሪ ያንብቡ
በመገናኛው መስክ ስንሄድ ቴክኖሎጂ ሰዎች በፈጣን የመልእክት መላላኪያ መድረኮች፣ እንደ ኢሜል እናም በማህበራዊ አውታረ መረቦች በቀላሉ እና በፍጥነት እንዲግባቡ አስችሏቸዋል። እንደዚሁም ቴክኖሎጂ ራሳችንን የምናዝናናበትን መንገድ ለውጦታል፣ የሙዚቃ እና የቪዲዮ ዥረት አገልግሎቶችን በመፍጠር እና በኦንላይን የሚደረጉ የቪዲዮ ጨዋታዎች ተወዳጅነት እንዲኖራቸዉ ረድቱዋል ።
በስራው ዓለም ቴክኖሎጂ ሂደቶችን በራስ-ሰር እንዲሰሩ፣ የቴሌኮም ስራዎችን ለመስራት እና አዳዲስ ሙያዎችን እና የስራ እድሎችን ለመፍጠር ፈቅዷል። በተጨማሪም ቴክኖሎጂ ትምህርትን ቀይሯል, በኦንላይን ላይ የመማሪያ መድረኮችን በመፍጠር ተማሪዎች በቀላሉ በየትኛዉም ቦታ በመሆን ይሚሰጥን ትምሀርት ለመከታተል አመቺነት ተፈጥርዋል።.
ግን ቴክኖሎጂ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል? ቴክኖሎጂ በዕለት ተዕለት ተግባራችን የበለጠ ውጤታማ በዚሁም ምርታማ እንድንሆን አስችሎናል። በተጨማሪም የአካል ጉዳተኞችን የህይወት ጥራትለማሻሻል ረድቷዋል ዛሬ የአይን ማየት ችግር ያለባቸዉ መስሎችን አና ቀለማትን ለመለየት ችለዋል እንዲሁም በኦንላይን ከየትናዉም አካባቢ የሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶችን ማግኘት አስችሏል, ይህም ሥር የሰደደ በሽታዎችን ለመቆጣጠር እና ለማከም ጭምር አስችሉዋል. .
ነገር ግን፣ ቴክኖሎጂ አዳዲስ ተግዳሮቶችን እና ችግሮችን አምጥቷል፣ ለምሳሌ የሞባይል መሳሪያዎች ሱስ፣ በኦንላይን ላይ ላልተገቡ ይዘቶች የመጋለጥ አደጋን ጋርጡዋል.
በማጠቃለያም ቴክኖሎጂ ህይወታችንን ጉልህ በሆነ መልኩ የለወጠ እና እየለወጠ ያለ ሃይለኛ መሳሪያ ነው። በህብረተሰባችን ላይ ያለውን ተጽእኖ ተረድተን በሃላፊነት ተጠቅመን ጥቅሞቹን ለመጠቀም እና ስጋቱን ለመቀነስ አስፈላጊ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነዉ ።የንባብን ባህልን ማዳበር
በላቀ እና ተከታታይ ዲጂታይዜሽን ምክንያት የማንበብ ልምድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆል ይገኛል ነገር ግን የመጽሃፍ ገፆችን መፈተሽ እና በጥልቀት ማንበብ ልዩ እና የሚያበለጽግ ተሞክሮ ይሰጣል። በተጨማሪም መፅሃፍ በስጦታ መስጠት ከቀላል ምልክት ያለፈ ለግንኙነት እና ለማደግ እድል ይሰጣል። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ መጽሐፍን የማንበብ ክህሎትና እና ለምን መጽሃፍን በስጦታ መሥጥት ጠቃሚ ተግባር እንደሆነ እናያለን ።.
የማንበብ ጥቅሙ ምንድን ነው?
መጽሐፍ ማንበብ የዩንቨርስን በር እንደ መክፈት ነው። በታተሙ ቃላቶች አማካይነት፣ ያለፉ ጊዜዎችን እና ቦታዎች ወደ ሁዋላ በጣም ሩቅ በመጉዋዝ የነበሩ ሁኔታዎችን ለመገንዘብ እና እንዲሁም የወደፊት እይታን አሻግሮ ለማይት የሚያስችል ይሆናል ።

የህዳሴ መጠናቀቅ
የህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ አባይ ወንዝ ላይ እየተገነቡ ካሉት የአፍሪካ ግዙፍ ግድቦች አንዱ ነው። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዓላማ በሀገሪቱ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚኖሩ ከ60 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን ለማብራት ኤሌክትሪክ ማመንጨት ነው። በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ምርት ወደ ጎረቤት አገሮች ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ተጨማሪ ያንብቡ
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያውያን ኪስ ብቻ የተሽፈነ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የሚገኝ ሲሆን 90 በመቶው ተጠናቋል። የጎረቤት ሀገራት ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና ዘላቂ እና ፍትሃዊ የሀብት አጠቃቀምን ለማረጋገጥ በጋራ መስራት ወሳኝ ነው። ይህም አሳሳቢ ጉዳዮችን ለመፍታት እና አካባቢን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ሁሉንም ሀገራት የሚጠቅሙ መፍትሄዎችን ለመፈለግ ቀጣይነት ያለው ውይይት እና ድርድር ይጠይቃል።
አርትፊሺያል ኢንተለጀንስ/ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ/
ግን ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ ምንድነው?
ዛሬ አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ በሁሉም ሰው ደጃፍ ላይ ደርሰዋል ለዚህም እንደ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉት ጥቂቶቹ እንደ GPT፣ BERT፣ GPT-2 ወይም Amazon Alexa የቻት ቋንቋ ሞዴሎችን መጥቀስ ይቻላል ..
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በተለምዶ የሰውን የማሰብ ችሎታ የሚጠይቁ ተግባራትን ማከናወን የሚችሉ ስርዓቶችን እና ፕሮግራሞችን በመፍጠር ላይ የሚያተኩር የኮምፒዩተር ሳይንስ ክፍል ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ
የተለያዩ አይነት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማለትም አነስ ያሉ AI ሲስተሞች፣ የተወሰኑ እና የተገደቡ ተግባራትን ሊያከናውኑ የሚችሉ ሲሆኑ ፣ ጠንካራ AI ሲስተሞች፣ የተለያዩ ውስብስብ ስራዎችን ለመስራት እና ከተለያዩ ሁኔታዎች ጋር መላመድ የሚችሉ ናቸው።AI በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በመድሃኒት፣ ሮቦቲክስ፣ የኢንዱስትሪ አውቶሜሽን፣ የደህንነት፣ ግብይት እና ሌሎችንም ጨምሮ ጥቅም ላይ ይውላል። አንዳንድ የተወሰኑ አፕሊኬሽኖች የህክምና መመርመሪያ ስርዓቶች፣ የኢንዱስትሪ ሮቦቶች፣ ቻትቦቶች እና ምናባዊ ረዳቶች፣ የማጭበርበር ማወቂያ ስርዓቶች እና የአሁናዊ መረጃ ትንተናም ያካትታሉ።አንዳንድ በጣም ከተለመዱት የ AI ቴክኒኮች መካከል የማሽን መማር፣ የኮምፒዩተር እይታ፣ የተፈጥሮ ቋንቋ ሂደት፣ እቅድ እና አስተሳሰብ፣ የነርቭ ኔትወርኮች እና ምሳሌያዊ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያካትታሉ።
የእስፔንና የኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ ግንኙነት
በኢትዮጵያና እና በስፔን ያለዉ ዲፕሎማስያዊ ግንኙንት በ1950ዎቹ በተለይም በ1951 የስፔን መንግስት በግብጽ የሚገኘዉን የስፔን ዉክልና በኢትዮጵያ የቆንሱላ ጉዳዮችን በአደራ ሰጥቶ ነበር። ተጨማሪ ያንብቡ
አቦል ቡና ጠጡ
በኢትዮጵያ ቡና የማፍላት ባህላዊ ሂደት የሚጀምረው የቡና ፍሬውን በእጅ በማጠብ እና በብረምጣድ በመቁላት ነው። ከዛ በኋላ በእጅ በተሰራ የእንጨት ሙቀጫ በመጠቀም ይፈጫሉ የቡናዉ መጠን ለዚህ ሥነ ሥርዓት በተሰበሰቡ ሰዎች ብዛት መጠን ይለካል።
የስፔን አርክቴክቸር በእኔ ካሜራ


