ወደ ሰመጠችው መርከብ ያቀኑት 5ቱ የጉብኝት

ወደ ሰመጠችዉ ታይታኒክ በ OceanGate TITAN የተጉዋዙት 5ቱ የጉብኝቱ አባላት እስካሁን አድራሻቸው አልተገኘም።

በአትላንቲክ ውቅያኖስ 4000 ሜ ጥልቀት ወደ ሰመጠችው  ታይታኒክ  መርከብ በ OceanGate TITAN ያቀኑት 5ቱ የጉብኝት ቡድኞች አባላት እሑድ 06-20-2023 ግንኙነታቸዉ ከተቅዋረጠ ጀምሮ እና  ዜናዉ በሰፊዉ  ከተሰራጨ በኋላ እስካሁን አልተገኑም ፍለጋው ቀጥሏል ።

በ1912 በአትላንቲክ ዉቅያኖስ የሰመጠችዉ ታይታኒክ መርከብ

ታይታኒክ ከኤፕሪል 14-15 ቀን 1912 በመጀመሪያ ጉዞዋ በአሳዛኝ ሁኔታ የሰጠመች ታዋቂ የብሪታኒያ የመንገደኞች መርከብ ነበረች።በዚያን ጊዜ ከተሰራው እጅግ በጣም ትልቅ እና የቅንጦት መርከብ ተደርጎ ይወሰድ ነበር።

ታይታኒክ ከሳውዝሃምፕተን እንግሊዝ ተነስቶ ወደ ኒውዮርክ ዩናይትድ ስቴትስ በማቅናት ጉዞዉን ጀመረ ። ሆኖም፣ በጉዞ ላይ እያለ በሰሜን አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ካለው የበረዶ ግግር ጋር በመጋጨቱ የመስመጥ አደጋ ደረሰበት  መርከቧ ለተሳፋሪዎች እና ለመርከቡዋ ሰራተኞች በቂ የህይወት ጀልባዎች ቢታጠቅም ለሁሉም የሚበቃ ባለመሆኑ የሰው ህይወት ጠፍቷል።

የታይታኒክ መርከብ መስጠም ወደ 1,500 የሚጠጉ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፣ይህም በታሪክ ከታዩት እጅግ ገዳይ የባህር አደጋዎች አንዱ ያደርገዋል። በአሁኑ ጊዜ የሰመጠችው ታይታኒክ መርከብ በአትላንቲክ ባህር ውስጥ 4000.ሜ ጥልቀት ላይ ትገኛለች.

ባለፉት አመታት ታይታኒክ የበርካታ መጽሃፎች፣ ፊልሞች እና ዘጋቢ ፊልሞች ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል፣ ይህም የዚህ አሳዛኝ ታሪክን ቀልብ እንዲስብ አድርጎታል።

በ1912 በአትላንቲክ ዉቅያኖስ የሰመጠችዉ ታይታኒክ መርከብ

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

error: Content is protected !!
Scroll to Top