የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የግማሽ ክፍለ ዘመን ህልም እውን ሆነ
የትውልድ ቅብብሎሽ
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የግማሽ ክፍለ ዘመን ህልም እውን ሆነ
ከኃይለ ሥላሴ ራዕይ እስከ አፍሪካ ትልቁ የውሃ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ድረስ ትዉልድ ሲቀባበለዉ የነበረዉ የአባይ ግድብ ግንባታ ፍጻሜዉ ተበስሩዋል። ከ50 ዓመታት በፊት የተፀነሰው GERD የፋይናንሺያል እና ዲፕሎማሲያዊ እንቅፋቶችን በማሸነፍ በቅርቡ ግንባታዉ ተጠናቆ ተመርቁዋል በዚሁም 5,000MW ኤሌክትሪክ በማምረት የኢትዮጵያን የኤሌክትሪፊኬሽን እድገት ለማሳደግ ይረዳል።
የግማሽ ክፍለ ዘመን ህልም እውን ሆነ
አሻራችን ታተመ፣ እንኩዋን ደስ አላችሁ
ህዳሴ ግድብ አባይ /ብሉ ናይል/ ተብሎ በሚጠራው ወንዝ ላይ ይገኛል።
ግድቡ 270 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሰው ሰራሽ ሀይቅ አለው።
74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ይዞ ይገኛል ።
ግድቡ 13 ተርባይኖች ያሉትና 5150 ሜ/ዋ የኤሌክትሪክ ሃይል ያመርታል።
በኃይለ ሥላሴ ዘመን የተወለደ ህልም
ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሀገሪቱን ኢንዱስትሪያላይዜሽን ለማነሳሳት በአባይ ወንዝ (ሰማያዊ አባይ) ላይ ግዙፍ ግድብ የመገንባት ሀሳብ አቅርበው ነበር። የገንዘብ እጥረት፣ ዲፕሎማሲያዊ ችግሮች እና ጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ይህንን ሃሳብና ፕሮጀክቱን ለአስርት አመታት እንዲራዘም አስገድደውታል።


በኢትዮጵያ የኤሌክትሪፊኬሽን ከፍተኛ ችግርና ፈተና ሆነ
ለብዙ አሥርተ ዓመታት የሀገሪቱ ጉልህ ክፍል በተለይም የገጠር አካባቢዎች ሆኑ ማምረቻ ቦታዎች እንዲሁም መኖሪያ ቤቶች ንግድ ቤቶች አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አልነበራቸውም የተገደበ የኤሌክትሪክ ሽፋን በጤና አጠባበቅ፣ በመማር እና በንፁህ ውሃ ተደራሽነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።
በዚሁም ንፁህ ኢነርጂ ማመንጨት ሀገራዊ ቀዳሚ ጉዳይ ሆነ ።

እንዴት ሊሆን ቻለ፡ ህዝብ እና መንግስት ቅንጅት

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዳግም የተወለደ ሲሆን ልዩ በሆነ መልኩ ከሃገር ዉጭና በሃገር ዉስጥ የተለያዩ መድረኮችን በመጠቀም በፋይናንስ የተደረገው ትብብር ከህዝቡ የበጎ ፈቃድ ቦነስ እና በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ዜጎች እና ለግድቡ የተመደበ የመንግስት ገንዘብ ነው።
GERD ከኢንጂነሪንግ እሴቱ ባሻገር፣ የትብብር የነጻነት እና የሀገር ኩራት ምልክት ሆኖ ይኖራል።
ዲፕሎማሲ እና ፈተናዎች
በ GERD የግንባታ ሂደት ከአባይ ተፋሰስ ሀገራት ጋር ውስብስብ አስቸጋሪና ያልተቁዋጩ ውይይቶች በጋር በትይዩ መድረኮች ተካሂደዋል ።
በሃገራቱ መካከል በፍሰቱ ስጋት እና የክልላዊ ቅንጅት ጉዳይ በቀጣይነትም ውይይት ያስፈልጋል።
ኢትዮጵያ ለህዝቦቿ የኃይል ዋስትና የመስጠት እና የኢነርጂ ትብብርን ማሳደግ እንዳለባት አረጋግጣለች።
በተፋሰስ ውስጥ የጋራ ጥቅሞችን ለማረጋገጥ የውይይት መድረኮች።

በዚህ ሰፊና ተደራሽነት ባለዉ ተፋሰስና በተፋሰስ ውስጥ የሚኖሩ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ የሚደርሰውን ጉዳት እያጤኑና እየፈቱ በየጊዜው በመወያየት ለጋራ ጥቅም መፍታት አለባቸው።
በተፋሰስ ውስጥ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ኑሯቸውን አሻሽለው የውሃ ቀዳሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ለአየር ንብረት ለውጥና ለአካባቢ ጥበቃ የሚውሉ ብከላዎችን መከላከል ይገባል።
አቅም እና ተፅዕኖ
5150 ሜ/ዋት አቅም ያለው GERD የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትን ያሳድጋል በሃገር ዉስጥ ያለዉን ፍላጎት በማሻሽል እና ኤሌክትሪክን ወደ ጎረቤት ሀገራት ለመላክ እድሎችን ይከፍታል፣የክልላዊ ውህደትንም ያጠናክራል።

በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች መካከል ጥቂቶቹ።
| Presa | País(es) | Río | Capacidad (MW) | Año de inicio de operación* |
|---|---|---|---|---|
| Tres Gargantas | China | Yangtsé | 22.500 | 2012 |
| Baihetan | China | Jinsha | 16.000 | 2022 |
| Itaipú | Brasil–Paraguay | Paraná | 14.000 | 1984 |
| Xiluodu | China | Jinsha | 13.860 | 2014 |
| Belo Monte | Brasil | Xingu | 11.200 | 2016 |
| Guri (Simón Bolívar) | Venezuela | Caroní | 10.235 | 1978 |
| Tucuruí | Brasil | Tocantins | 8.370 | 1984 |
| Wudongde | China | Jinsha | 10.200 | 2021 |
| Grand Coulee | Estados Unidos | Columbia | 6.809 | 1942 |
| Sayano–Shushenskaya | Rusia | Yeniséi | 6.400 | 1978 |
| Tarbela | Pakistán | Indo | 4.888 | 1976 |
| GERD | Etiopía | Abay (Nilo Azul) | 5.000 | — |

Leave a Comment